ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ጠዋት የፌደራላዊት ጀርመን የኢኮኖሚያዊ ትብብር ሚኒስትር የሆኑትን ዶ/ር ገርድ ሙለርን እና የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑትን ሚስተር ሁበርተስ ሄሊን በእንግድነት ተቀብለዋል። ይህ የከፍተኛ አመራሮች ጉብኝት ከጥቂት ሳምንታት በፊት በበርሊን ከተካሄደውን የጂ20 ኮምፓክት አፍሪካ ኮንፈረንስ የተከተለ ሲሆን፣ በወቅቱም ኢትዮጵያና ጀርመን የግሉን ዘርፍ ኢንቨስትመንት እና ዘላቂ የኢኮኖሚ ልማትን ለማበረታታት በለውጥ አጋርነት ላይ ስምምነት መፈራረማቸው የሚታወስ ነው። ስምምነቱን እውን ለማድረግ የሁለትዮሽ ውይይት ከተካሄደ በኋላ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጀርመን በኢትዮጵያ የለውጥ አጋርነትን እንዲሁም ቀጣይ የትብብር ማዕቀፍን ለማስቀጠል 352.5 ሚሊየን ዩሮ የለገሰችበትን ስምምነት አፈራርመዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በተጨማሪም የግብርናን ዘዴ ለማሻሻል ይረዳ ዘንድ ድጋፍ እንዲደረግ በጠየቁት መሠረት የጀርመን መንግሥት የለገሳቸው መለዋወጫ የተሟላላቸው የ144 የግብርና መሣሪያዎችን ቁልፎች የርክክብ ሂደት በሚመለከታቸው አካላት መካከል አስፈጽመዋል።
ዶ/ር አብይ አህመድ የጀርመን የኢኮኖሚያዊ ትብብር ሚኒስትር የሆኑትን ዶ/ር ገርድ ሙለርን እና የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑትን ሚስተር ሁበርተስ ሄሊን ጋር ተወያዩ Read More
ክቡር አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ ከጀርመን ልኡካን ጋር ተወያዩ Read More
5ኛው የኢትዮጵያ፣ የሱዳንና የግብፅ የውሃ ጉዳይ የሚኒስትሮች ስብሰባ በካይሮ መካሄድ ጀመረ Read More
የኢትዮጵያ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን የዩጋንዳ ቆይታውን በማጠናቀቅ አዲስ አበባ ገባ ==================================================== Read More
የመጋቢት 06 ቀን 2011 ዓ.ም የቃል አቀባይ ጽ/ቤት - ሳምንታዊ መግለጫ Read More